ኦቲዝም /Autism 


ልጅዎ ከሚከተሉት ምልክቶች አንዱን ያሳያል/ታሳያለች ወይ?


1. 12 ወራት ቢሆነውም/ቢሆናትም መኮላተፍም እንኳን የለም

2. ከ 12 ወራት ቢሆነውም/ቢሆናትም  ለማመልከት፣ ለማሳየት፣ ለመድረስ፣ ወይም እጅን አለማወዛወዝ 

3. 12 ወራት ቢሆነውም/ቢሆናትም በስም ሲጠሩ(ሯ)ት ምላሽ  አለመስጠ24 ወራት ቢሆነውም/ቢሆናትም ምንም ቃል አለመናገር

4. በማንኛውም እድሜ የመናገር፣ የመኮላተፍ ወይም የማህበራዊ ችሎታዎች መጓደል/መጥፋ

5. ከእቃዎች ወይም ከመጫወቻ አካሎች ጋር ብዙ ግዜ ማሳለፍ

6. ያልተለመዱ እንቅስቃሴዎች ወይም ትግባሬዎች ድግግሞሽ


ልጄ ኦቲዝም እንዳለዉ ስጠረጥር ምን ማድረግ አለብኝ?


እንደ ወላጅ ለልጅዎ የሚገባዉን እርዳታ ለማግኘት ስለሆነ በሃሳብዎ ይተማመኑ!!


  • የ ልጅዎን ሃኪም ወይም እርዳታ ወደ ሚሰጠዉ ሃኪም ቤት በአስቸኳይ ልዩ ኦቲዝም ምርመራ እንዲደረግለት (ላት) መጠየቅ ያስፈልጋል።

  • ልጅዎ ከሶስት ዓመት በታች ከሆነ በአካባቢዎ (ባሉበት ከተማ )ቀደም ብሎ (በሽታዉ ሳይብስ) ምርመራ እርዳታ ወደ ሚደረግበት ቦታ መዉሰ

በጣም አስፈላጊ ነው። በቴክሳስ የሚገኘዉ ኢሲአይ ( ECI) ወደሚባለዉ መሔድ ያስፈልጋል ። 1(800)628-5115 ደዉሉ

  • ልጅዎ ከሶስት ዓመት በላይ ከሆነ ለወደፊት ልጅዎ ሚማርበት ትምህርት ቤት ባስቸኳይ ልዩ ትምህርት ወደ ሚሰጥበት ከፍል እንዲገባ በመጠየቅ ተገቢዉን እርዳታ ማግኘት ይቻላል።
  • ቀደም ብሎ (በሽታዉ ሳይብስ) ምርመራ እርዳታ ወደሚደረግበት ቦታ መዉሰድ ክትትል በማድረግ ላኦቲዝም መፍትሔ ማግኘት ይቻላል።


እባክዎትን ችላ አይበሉ!!!!!


በተቻለ መጠን ልጅዎ ቀደም ብሎ (በሽታዉ ሳይብስ) ምርመራ በማድረግ ልጅዎ ወዳ ዕመርታዉ ( ወደ ታሰበበት ግቡ) ይደርሳል።