የምስራቅ አፍሪቃን ልጆችና ቤተሰቦች ማግኘትማንነታችን

RFASG ቤተስቦች በዳላስ/ፎርትዎርዝ አካባቢ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ልጆችን የሚያሳድጉ በአላማቸው የፀኑ ቤተሰቦች የድጋፍ ቡድን ነው። ቡድን ውስጥ ያሉ አብዛኛዎቹ ቤተሰቦች ከምስራቅ አፍሪቃ የፈለሱ ናቸው። ቡድኑ የተመሰረተው ባንዲት ኦቲዝም ያላቸ ልጆች ያላት አንዲት ነርስ ነው።ራእያችን

በህብረተሰባችን ልዩ ፍላጎት ያሏቸው ልጆችን ወደ ሚያሳድጉ ቤተሰቦች ለመድረስ እና እነሱን ለማጠናከር ልጆቻቸውንም የተሟላ እምቅ ችሎታቸውን እንዲጨብጡ ማገዝ።
አላማችን

 • ለልጆቻቸው አገልግሎቶችና መገልገያዎች እንዲያግኙ ቤተሰቦችን ማስተማር፣ መደገፍና እና ማበረታታት
 • ስለ ስንክልና ላላቸው ልጆችና ቤተሰቦቻቸው በመቆም በማህበረስባችን ውስጥ
 • የልጆችንና የቤተሰቦቻቸውን ፍላጎቶች ለማግኘት ከአገልግሎ አቅራቢዎች፣ መምህራን፣ ጤና አቅራቢዎች እና ድርጅቶች ጋር አብሮ መስራት
 • በማህበረሰባችን ውስጥ ስለ ኦቲዝም እና ሌሎች የእድገት ስንክልናዎች ህዝባዊና ሙያዊ ንቃት ማዳበር

 


የምንሰራው

 • ልዩ ፍላጎቶች ያሏቸውን ልጆች የማስደግ የተለያዩ መስኮች ላይ ለቤተሰቦች በባህል የበለፀገ ድጋፍ ማቅረብ
 • ቤተሰቦችን በጉዟቸው ማበረታታት
 • ወርሀዊ ትምህርታዊ ክውንውቶች በማስተናገድ ቤተሰቦችን በተለያዩ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ልጆች ማሳደጊያ መስኮች ማስተማር
 • ውጤታማ በሆኑ መንገዶች ለልጆቻቻው እንዲቆሙ/እንዲከራከሩ ለምከራከርና ለመምራት ቤተሰቦችን ወደ ARD እና ሌሎች ድርጅቶች ማጀብ
 • በቃል መረጃዎችን በመተርጎም እና ሰንዶችን በመተርጎም ቤተሰቦችን ማገ
 • ቤተሰቦች ተፈላጊ ህክምናዎች፣ ጣልቃገብነቶች፣ እና መክር ለመድረስ/ለማግኘት ለማገዝ ህዝባዊ/የግል አቅራቢዎች ዝርዝር ማቅረ
 • ለተፈላጊ አገልግሎቶች የሚሆን ገንዘብ ፍለጋ ላይ ቤተሰቦችን ማገ
 • ቤተሰቦች አስፈላጊ የት/ቤት፣ የህክምና፣ እና ሌሎች ዘገባዎችን አደራጅተው እንዲንከባከቡ ማስተማር፣ በማህበረሰብ ክውነቶች በመሳተፍ ስለ ኦቲዝም እና ስለ ሌሎች የእድገት ስንክልናዎች ንቃት ማዳበር።ሌሎች ፕሮጀክቶች

ኛ ንቃት ለማዳበር እና ልዩ ፍላጎቶች ያሏቸው ልጆችንና ቤተሰቦቻቸውን ለመደገፍ ከፕሮጀክቶች፣ ድርጅቶች፣ እና በኢትዮጵያና በኤርትራ ከሚገኙ ት/ቤቶች ጋር እንሻረካለን።